ጠቅላላ

General

ወዳንቺ የመጣው

Lyrics

ወዳንቺ የመጣው በብሩህ ደመና

ከሦስቱ አካል አንዱ ክርስቶስ ነውና

የጠፋ በግ አዳም ታደሰ በጌታ

በአንቺ ተፈጸመ የሰው ልጆች ደስታ

በደይን የተጣለች ሄዋን ተደሰተች

የደስታ መፍለቂያ አንቺን ስላገኘች

የበረከት ፍሬ ካንቺ ተገኘልን

የወይን ቦታ ነሽ ድንግል እናታችን

ወልድም ባህሪሽን ባህሪ አድርጎት

ለፍጥረታት ጌታ መዓዛሽ ተስማምቶት

ካንቺ ይወለድ ዘንድ ፍጹም ሊላላክሽ

በጥቂቱ አደገ ተልኮና ታዞሽ

ከድንግልና ጋር አንድ የሆነ ሀሊብ

በሩካቤ ሳይሆን በብስራት እንደ ንብ

ከሆድ መጥበብ ጋራ የመለኮት ስፋት

እንቺ ሆነሽ ሳለ ታናሿ ሙሽሪት

በፍጡር ህሊና የማይመረመር

እፁብ ነው ድንቅ ነው የመጽነሷ ነገር

እሳት ወነበልባል በሆድሽ ውስጥ ሲያድር

ነደ ነበልባሉ አልፈጀሽም ነበር

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening