✦
ጠቅላላ
•General
እንዴት ብለህ
Lyrics
እንዴት /2/ ብለህ ተገኘህ እኔ ቤት /2/
እንዴት አልሰለቸህ መተኛት ከበረት /2/ እንዴት
አበሰሩን መላእክቱ ተወለደ ሂዱ እያሉ
ግርግም መሃል ተጠቅልሏል የምስራች ለአለም ሁሉ
ተነስቼ ገሰገስኩኝ ከበጎች ጋር ከበረት
የማይንቀኝ መድሃቱን አይኔ አየችው በሊሌት
ቀና ስል ከሰማይ ኮከብ ይመራኛል
የፍቅሩ መዓዛ ልቤን ይጠራኛል
እንደ አጭሩ ቀራጭ ሾላ ላይ ብወጣ
ከቤቴ ሊገባ መምህሩ መጣ እንዴት
ፈሪሳዊው ቢጸየፈኝ አመንዝራ ቀራጭ ብሎ
አልፎኝ ሲሄድ ያ ሌዋዊ ተጸይፎ ተነጥሎ
አግሬን ሲያጥብ ተመልከቱ በኔ ምትክ ሲሰቀል
ይሄን ብርቱ ፍቅር እዩ አለም ሁሉ ጉድ ይበል
ቀና ስል ከሰማይ ኮከብ ይመራኛል
የፍቅሩ መዓዛ ልቤን ይጠራኛል
እንደ አጭሩ ቀራጭ ሾላ ላይ ብወጣ
ከቤቴ ሊገባ መምህሩ መጣ እንዴት
እኔ ማን ነኝ የምትገባ ከጣሪያዬ ከቤቴ ስር
እሰማለሁ እድናለሁ ጌታዬ ሆይ ቃል ተናገር
አቴርሳታ የኔ ገዢ የኑሮዬ የመንገዴ
የማይቀሙኝ በጎ እድሌ እኔ ባንተ መውደዴ
ቀና ስል ከሰማይ ኮከብ ይመራኛል
የፍቅሩ መዓዛ ልቤን ይጠራኛል
እንደ አጭሩ ቀራጭ ሾላ ላይ ብወጣ
ከቤቴ ሊገባ መምህሩ መጣ እንዴት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.