ጠቅላላ

General

በኤፍራታ ምድር

Lyrics

በኤፍራታ ምድር /በቤተልሔም/ /2/

ጌታ ተወለደ /ከድንግል ማርያም/ /2/

ብርሃናዊው ኮከብ /ከሰማይ ዝቅ አለ/ /2/

ፍጥረትም ዘመረ /ሃሌ ሉያ እያለ/ /2/

መንጋውን በሌሊት ሲጠብቁ እረኞች

ከሰማይም ሰሙ ታላቅ የምስራች

በመላአክቱ ግርማ ምድር ስታበራ

የሚያስጨንቅ ነበር እጅግ የሚያስፈራ

ድንገትም የሰማይ ሰራዊት ተገልጠው

ባንድነት ዘመሩ ከኖሎት ጋር ሆነው

ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ብለው

ሰላምም በምድር በጎ ፈቃድ ለሰው

ቤተልሔም ሄደው ጌታን ተሳለሙት

ከእናቱ ጋር ሆኖ በግርግም አገኙት

የመላእክትን ዜና እረኞች አወሩ

በልዩ ምስጋና አምላክን ሲያከብሩ

ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ፍስሐ ደስታ

በዳዊት ከተማ ተወለደ ጌታ

ሕፃን ከእናቱ ጋር በግርግም ፈልጉት

እርሱ ነው ለሰዎች የድኅነት ምልክት

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening