ጠቅላላ

General

ደስ ይበለን

Lyrics

ደስ ይበለን እልል በሉ/2/

አልቀረም ተቀብሮ ተገኘ መስቀሉ/2/

በብርሃን መላት ዓለምን በሙሉ/2/

አ.ዝ

ምን ቢታገሉ ምቀኞች ቢጥሩ/2/

ቅዱስ መስቀሉንም ሸሽገው ቢሰውሩ/2/

አልቻሉም ሊያጠፉት ምን ቢተባበሩ/2/

አ.ዝ

በተራራ ተሰውሮ ለዘመናት/2/

ተጥሎ በተንኮል ተደብቆ ከኖረበት/2/

ተከሰተ ዛሬ በደመራ እሳት/2/

አ.ዝ

እሌኒ ነች ይህን ምስጢር ያስገኘችው/2/

ደመራን በቦታው በክብር ያስቆመችው/2/

የተንኮልን ተራራ ያስቆፈረቸው/2/

አ.ዝ

ታሪካዊ የክርስቶስ ሕያው መስቀል /2/

ተገለጠ ዛሬ በክብር በግሩም ሀይል/2/

በክብር ምን ግዜም እንዲህ ያበራል /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening