ጠቅላላ

General

ቤተክርስቲያን

Lyrics

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት/2/

አትመረመርም/2/ እጅግ ጥልቅ ናት

በስጋዊ ጥበብ ለማወቅ ሲቃጣ

እምነት መነፀሩን ይዞ ስላልመጣ

ሰው ሁሉ በክህደት /2/ ፈጣሪውን አጣ

የመስቀሉ ቃል ለኛ የእግዚአብሔር ሀይል

ነው/2/

ለማያምኑት ሞኝነት ነው ለእኛ ግን ህይወት

ነው

እንመሰክራለን አማኑኤል አለ

እንመሰክራለን ፈጣሪያችን አለ

አንዳንዱ ቢክደው/2/ እየተታለለ

እንመሰክራለን ድንግል አማላጅ ናት

እንመሰክራለን ማርያም አማላጅ ናት

ወላዲተ አምላ/2/ መሠረተ ሕይወት

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening