ጠቅላላ

General

መስቀል ተመርኩዘን

Lyrics

መስቀል ተመርኩዘን ወንጌል ተጫምተን

ሀይማኖትን ሰብከን በክርስቶስ አምነን

ማን ያሸንፈናል እኛ ክርስቲያን

ክርስቶስ አለልን

አ.ዝ

ንግስቲቷ እሌኒ በጣም የታደለች

በእጣን ጢስ ተመርታ መስቀሉን አገኘች

መድሃኒት ስትፈልግ ኪራኮስን ይዛ

መስቀሉን አገኘች የዓለሙን ቤዛ

አ.ዝ

ሙታንም ተነስተው ያመሰገኑት

እፀ መስቀሉ ነው የኛ መድሃኒት

መስቀል ምርኩዛችን ጎዳናው ወንጌል

ወደ ገነት እንጂ አንገባም ሲኦል

ንዑ ንወድሶ ለዕፀ መስቀል

የተሸከመውን የዐምላክን ቃል

ንዑ ንወድሳ ለማርያም ድንግል

አክሊለ ምዕመናን ምክሀ ደናግል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening