✦
ጠቅላላ
•General
ለዕፀ መስቀሉ እንስገድ
Lyrics
ለዕፀ መስቀሉ እንስገድ
ጠላት እዲጠፋ እንዲሆን አመድ
ዕፀ መስቀሉን ያዙ ጋሻ
ሠይጣን እንዲጠፋ እንዲያጣ መድረሻ
ዕፀ መስቀሉን ተሳለሙ
ያምላክ ሀይል ያለበት ደመ ማህተሙ
መስቀል ሀይል ነው ለክርስቲያን
እሱን የያዘ ሰው አይደፍረውም ሠይጣን
ዕፀ መስቀሉን እንጠጋ
ተሰባብሮ እንዲወድቅ የዲያቢሎስ መንጋ
ዕፀ መስቀሉ ያኮራናል
እሱን ከተጠጋን ሠይጣን ይፈራናል
መመኪያችን ነው መስቀል
ተቀርጿልና በመለኮት ኃይል
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.