ጠቅላላ

General

አምላክ ሰው ሆነ

Lyrics

አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ

በድንግል ማርያም ተከናወነ

አ.ዝ

የአብ ሙሽራ የወልድ እናቱ

የመንፈስ ቅዱስ ፅርሀ ቤቱ

በሰማይ ሆኖ አብ አፀናሽ

ወልድም ለራሱ ቤት አረገሽ

መንፈስ ቅዱስ ነው/2/ የፀለለሽ

ከሦስቱ አካል ወልድ አንዱ አካል

መጣ ወረደ በገባው ቃል

ተፀንሶ ሳለ ወልድም ከእናቱ

አልተነጠለም ከሦስትነቱ

ታምራት አርጓል ድውይ ፈውሷል በአምላክነቱ

አ.ዝ

ይህን ድንቅ ምስጢር በሉ ግሩም

ምስጋና አቅርቡ ለዘለዓለም

በሥነፍጥረት ይታወቃል

የዓለም ፈጣሪ የእግዚአብሔር ቃል

ደስ ይበላችሁ ደስ ይበለን በሉ እልል

አ.ዝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening