✦
ጠቅላላ
•General
ይኸው ተወለደ
Lyrics
ይኸው ተወለደ የዓለምመድሀኒት/3/
እሠይ ተወለደ የዓለም መድሀኒት/3/
ትንቢት ተናገሩ ነቢያቱ ሁሉ/3/
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ/3/
አ.ዝ
ሰብአ ሰገል መጡ እጅ መንሻ ይዘው/3/
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው/3/
አ.ዝ
ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ/3/
አምላክ ቀዳማዊ ተወልዷል እያሉ/3/
አ.ዝ
ህፃናት እንሂድ ከልደቱ ቤት/3/
ውኃ ሆኗልና ማርና ወተት/3/
አ.ዝ
በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደ እንግዳ/3/
ብስራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ/3/
አ.ዝ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.