ጠቅላላ

General

አይኖቼ

Lyrics

አይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና/2/

ይገባዋል/2/ ክብርና ምስጋና

አ.ዝ

ከሰማይ ወረደ ሰውን በማፍቀር

ሀያሉ ጌታችን ቸሩ እግዚአብሔር

በቤተልሔም ዋሻ በዚያ በግርግም

ተወለደ ዛሬ መድኃኔዓለም

አ.ዝ

የተነበየለት በዙ ነቢያት

ከድንግል ተወልዶ አዳነን በእውነት

ከበደል ጉራንጉር አነሳን ከትቢያ

በአንድነት እንዘምር እንበል ሀሌ ሉያ

አ.ዝ

የተናቅን ስንሆን እኛን ሊያከብር ወዶ

በፍቅሩ አከበረን እራሱን አዋርዶ

ምን ዓይነት ፍቅር ነው ፍፁም ምህረት

የአምላክ መወለድ በከብቶች በረት

አ.ዝ

ዓለምን የሚያድን የሰዎች አለኝታ

አ.ዝ

በንፅህና ፀንተሸ ቤተመቅደስ የኖርሽ

በዕቱም ድንግልና መዳኒትን ወለድሽ

የዓለሙን ኃጢያት የሚያስተስርይ ጌታ

ተወልዷል ከድንግል የሔዋን አለኝታ

አ.ዝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening