ጠቅላላ

General

ጥምቀተ ባህር

Lyrics

ጥምቀተ ባህር ዮርዳኖስ ነይ/2/

ሀሌ ሉያ/4/

ጌታችን ሲጠመቅ ባህር ምን አለች

አልችለውም ብላ ወደፊት ሸሸች

እሳተ መለኮት በወንዙ ሲሞላ

ዮርዳኖስም ሸሸ ቀረ ወደ ኋላ

አብ ነበር የመጣው ደመናውን ጭኖ

መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሣል ሆኖ

ለልጁ ምስክር ሊሠጥ ፈለገና

ቃሉን ወረወረ ሆኖ በደመና

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening