✦
ጠቅላላ
•General
የዓለምን በደል
Lyrics
የዓለምን በደል የሠውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላዕክቱን ትቶ
ፅድቅን ለመፈፀም በደልን አጥፍቶ
የሠላሙ መሪ የሠላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ
የሰማዮች ሰማይ የማይችሉት ንጉሥ
ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደፈረስ
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
ልጁ በዮርዳኖስ ፅድቅን ሲመሠርት
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት
እንደምናነበው በወንጌል ተፅፎ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ አርፎ
በርግብ ምሳሌ ክንፉን አሰይፎ
ባህር ስትጨነቅ ተራራው ሲጨፍር
ሰማዩ ሲከፈት ደመናው ሲናገር
ዓለም በዛሬው ቀን አየች ይህን ምስጢር
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.