ጠቅላላ

General

ከድንግል ተወልዶ

Lyrics

ከድንግል ተወልዶ እኛን ሊቀድስ

ተጠመቀ ኢየሱስ በባህረ ዮርዳኖስ

መጥምቅ ዩሐንስ ምንኛ ታደለ

ከነቢያት ሁሉ ስልጣኑ ከፍ አለ

ትንቢቱን ለፈፅም አስቦ ክርስቶስ

ተጠምቆ አዳነን በባህረ ዮርዳኖስ

ምሥጢረ ሥላሴ ታየ የዚያን ለታ

በምን ይከፈላል የአምላክ ውለታ

እመቤቴ ማርያም እመቤቴ ሆይ

አንቺን ያመነ ሰው ይበደላል ወይ

እመቤቴ ማርያም ምንኛ ታደልሽ

ከአዳም ልጆች ሁሉ አንቺ ተመረጥሽ

ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለምን

ኑ እናመስግነው ባንድ ላይ ሆነን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening