✦
ጠቅላላ
•General
ተናገራ
Lyrics
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ/2/
እዝራ በመሰንቆ እያጫወታት
ሳታውቀው አለፈች ያን መልዐከ ሞት
ውኆች ቀለም ሆነው እንጨቶች ብዕር
ቢፅፉት አያልቅም የማርያም ክብር
የጠፋውን ሊያድን ወረደ ከላይ
የበጎች እረኛ አምላክ አዶናይ
ትንቢት ተናገሩ ነቢያቱ ሁሉ
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ
የአህዛብ አምላክ በማይሻር ቃሉ
ዛሬ ተሠበከ ለዓለሙ ሁሉ
ጌታ ተጠመቀ በዩሐንስ እጅ
ወገኖቹን ሁሉ በጥምቀት ሊዋጅ
ለብርሃናት ጌታ ቸሩ ፈጣሪያችን
ሀሌ ሀሌ ሉያ እንበል ሁላችን
እንዘምር/3/ ሁላችን
ለታላቁ ንጉስ ለመድሀኒታችን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.