✦
ጠቅላላ
•General
እሰይ እሰይ
Lyrics
እሰይ እሰይ ተወለደ
እሰይ እሰይ ተጠመቀ
ከሰማየ ሰማያት ወረደ
ከድንግል ማርያም ተወለደ
እሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ
ቸሩ አባታችን
እሱ ባይጠመቅ
መድሀኒታችን
መች ትገኝ ነበረ
ገነት ምድራችን
ብርሃን ወጣላችሁ እሰይ አሰይ
የእውነት ወገኖች
በጨለማ ጉዞ
እንዳንሰለች
እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ
አንድያ ልጁን
እርሱ ወድዷልና
እንዲሁ ዓለሙን
እንደ ጠል ወረደ
እሰይ እሰይ
ከሰማይ ወደኛ
ወገኖቹን ሊያድን
ከክፉ ቁራኛ
ከሰማይ ወደኛ እሰይ እሰይ
ለወረደው ጌታ
ክብርና ምስጋና
ይድረሰው በዕልልታ
እንዘምር/2/ በእልልታ
ለታላቁ ንጉስ ለሠራዊት ጌታ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.