ጠቅላላ

General

ሰዎች ደስ ይበለን

Lyrics

ሰዎች ደስ ይበለን በአምላካችን

ከኃጢያት ባርነት ነፃ ላወጣን

ተነሱ እናመስግን ውለታው ብዙነው

ምን ይከፈለዋል ተመስገን ብቻነው

በኃጢያት በሽታ ወድቄ ሳለሁ

መድሀኒት ክርስቶስ ከውድቀቴ አነሣኝ

ስጦታህ ብዙ ነው ለኔ የሰጠኸኝ

አ.ዝ

ተመስገን ብቻ ነው አምላክ ላንተ ያለኝ

እንደ በርጠሚዎስ እውር የነበርኩኝ

ዛሬ ግን በአምላኬ ድህነት አገኘሁኝ

ሕጉ ለመንገዴ ብርሀን ሆኖኛል

የእርሱ ስለሆንኩኝ ሰላሙን ሰጥቶኛል

አ.ዝ

አ.ዝ

በድንቅ አጠራርህ በፍቅር የጠራኸኝ

ከአጋንንት እስራት ነፃ ያወጣኸኝ

አልፋና ኦሜጋ ዘልዓለም የምትኖር

ኤልሻዳይ የሆንከው አማኑኤል ተመስገን

የእዳ ደብዳቤውን ጌታ የቀደደው

የማዳኑን ስራ በዐይኔ አይቼዋለሁ

ቸርነቱ አያልቅም ድንቅ የሆነ ጌታ

ስሙን እናወድስ እንዘምር በእልልታ

አ.ዝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening