ጠቅላላ

General

የመላዕክት እህት

Lyrics

የመላእክት አለቃ ገብርኤል ላከው

ኃያሉ እግዚአብሔር በሰማያት ያለው

የባህርይ ልጄ ወዳንቺ ይመጣል

ብለህ ለጽዮን ልጅ ንገራት ለድንግል

አዝ

ኃይለ ልዑል ወልድም ስጋሽን ይለብሳል

በተለየ አካሉ ወደ አንቺ ይመጣል

ከስጋሽም ስጋን ከነፍስሽም ነፍስ ነስቶ ይዋሃዳል

በገጸ ህጻናት ከአንቺ ይወለዳል

አዝ

ደንቆሮ ሊሰማ ዲዶች ሊናገሩ

በጌታ ታምራት ዕውራን ሊበሩ

ሙታን ይነሱ ዘንድ በማህጸንሽ ፍሬ

ከእግዚአብሔር ወደ አንቺ ተልኬያለሁ ዛሬ

አዝ

ደስ አሰኛት አለው በልዩ ሰላምታ

ሀሴት እንድታደርግ ምሥራቹን ሰምታ

ድዳ እንዳደረከው ካህን ዘካሪያስን

እንዳታሳዝናት ከእርሷ ጋር ስትደርስ

አዝ

ገብርኤል በደስታ ምሥራቹን ይዞ

ከሰማይ ወረደ በአምላኩ ታዞ

በሊባኖስ መንደር እስኪሰማ ድረስ

ክንፉን እያማታ መጣ ሲገሰግስ

አዝ

ደስ ይበልሽ አላት እየተሳለማት

ሀርን ከወርቅ ጋር ስትፈትል አገኝቷት

እውነተኛው ንጉስ ከአንች ይወለዳል

ለአንች ፍቅርና አንድነት ይገባል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening