ጠቅላላ

General

የጻድቃን መመኪያ

Lyrics

የጻድቃን መመኪያ አምላክን የወለድሽ

ድንግል ማርያም ሆይ የተባረክሽ ነሽ

አማን በአማን/2/ የአምላክ እናቱ

ተማፅነናል በአንቺ ድንግል ወላዲቱ

ነቢያቱ ሁሉ እፁብ ናት ያሉሽ

ደመና ኤልያስ ድንግል አንቺ ነሽ

የመላእክት እህት የፃድቃን እናት

በአንቺ መመኪያነት አገኘን ህይወት

እሣቱ ሳይጠፋ ጫፏ ሳይቃጠል

ድንግል ማርያም ናት ሙሴ ያያት ቅጠል

ባለሟልነትን ካምላክ ያገኘሽ

ምህረት ለምኝልን ከአንዱ ከልጅሽ

የተዋህዶ ልጆች በአንድነት ሆነን

ሰአሊለነ ቅድስት እንልሻለን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening