ጠቅላላ

General

የብርሀን ጎርፍ ናት

Lyrics

የብርሀን ጎርፍ ናት ድንግል እናታችን

ከሰማይ እያበራች ደስአለው ልባችን

ፍቅርሽ ሰላምሽ ድህነት ይሁነን

ፍጥረት በሙሉ/2/ ፊትሽ ይወድቃሉ

ፀጋሽ ይድረሰን/2/ ይሰጠን እያሉ

የኔ ልብ ምን ፅድቅ አለው አንቺን ለማስተናገድ

የኃጢያት ጎተራነው የተመላ በስስት

ኧረ እንዴት ድንግል ትኑርበት

አትፀየፍም የኔን ልብ ታሰናዳዋለች

ስለ ኃጢያቴም የኔ እናት ምልጃ ታቀርባለች

ልባቸውን የዘጉ ድንግልን ለማስገባት

ህሊናቸው ይመለስ እንፀልይ ለዚህ ጥፋት

አምላክን ይዛነው ድንግል የምትመጣው

እርሷን ስመልስ ጌታን ነው የምናስቀይመው/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening