✦
ጠቅላላ
•General
አማናዊት እናት
Lyrics
አማናዊት እናት እነኋት ማርያም
ለቅዱስ ዩሀንስ ተሰጠች ለዓለም
ድህነት የምታሰጥ የዘለዓለም ህይወት
የእኛ ተስፋችን ኪዳነ ምህረት
ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስን
ተዋሀደ አምላክ እኛን ሊያድነን
አልተለየችም በማዳኑ ስራ እናታችን
ፅዮን ማርያም መጠጊያ ጥላችን
ወልዳ ያሳደገች አዝላ የተሰደደች
የጌታችን እናት ድንግል ተንከራተተች
ከእግረ መስቀሉ ከዙፋኑ በቀኝ ቆማለች
ትናንት ዛሬም ነገ ማርልኝ ትላለች
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.