ጠቅላላ

General

በምን በምን

Lyrics

በምን በምን አንመስላት ድግል ማርያምን/2/

ምሳሌ የላትም/2/ ክብሯን የሚመጥን/2/

የሙሴ ፅላት ነሽ የምህረት ቃልኪዳን

የአብርሃም ድነኳን

የያዕቆብ መሰላል

የብርሃን መውጫ

የኖህ ድንቅ መርከብ

የመላዕክት እህት

የብርሃን ርግብ/2/

የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር

የዕዝራ መሰንቆ

የጌድዮን ፀምር

ድንግል እመቤት ናት የፃድቃኖች በር

ሆና የተገኘች

የቅዱሳን እናት

ችላ ተሸከመች

ብርሀን ትሁነን

የአምላክ ማህደር/2/

የአለም ንግስት

መለኮተ ዕሣት

ጨለማን ገላልጣ

አማልዳ ታስምረን ከዚህ ዓለም ጣጣ/2/

ከማር ይጣፍጣል

አምላክን አቅፋለች

አለም ሁሉ የዳነው

እናታችን ፅዮን

የድንግል መዓዛ

በሁለት እጇ ይዛ

በልጅሽ ነውና

ይድረስሽ ምስጋና/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening