✦
ጠቅላላ
•General
የጠሩሽ
Lyrics
የጠሩሽ አንቺን ተማፅነው የዳኑብሽ
የበላዔ ሰብዕ እመቤት የአምላክ እናት
ድንግል አዛኝቷ ማርያም ቅድስት
በቃልኪዳንህ ብዙዎች ድነዋል
በምልጃሽም ፅድቅን አግኝተዋል
የአምላክ ቸርነቱን አይተዋል/2/
የዕሣትን ባሕር ባንቺ ተሸግረዋል
የሰይጣንን ጦር ባንቺ ድል ነስተዋል
ለሰማያዊው ክብር በቅተዋል/2/
ነፍሳቸውም ፅድቅን አግኝታለች
ሕይወታቸውም በአንቺ ትድናለች
ድንግል ሆይ አማልጂኝ ትላለች/2/
እኔም በአንቺ እታመናለው
የአምላክ እናት አማልጂኝ ብያለው
በአማላጅነትሽ እድናለሁ/2/
እኛም በአንቺ እንታመናለን
የአምላክ እናት አሳስቢ እንላለን
በአማላጅነትሽ እንድናለን/2/
ምዕመናንም ባንቺ ያምናሉ
የአምላክ እናት አሳስቢ ይላሉ
በአማለጅነትሽ ይድናሉ/2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.