ጠቅላላ

General

አምላክ ለእኛ ብሎ

Lyrics

አምላክ ለእኛ ብሎ ቢያፈሰው ደሙን

ለምን ከለከለች ፀሐይ ብርሃኗን

የከበረው ስጋ የከበረው ደም

በመስቀል ላይ ዋለ በኢየሩሳሌም

እዩት ኢየሱስን መስቀሉ ማማሩ

ለተመራመረው ብዙ ነው ምስጢሩ

ቢመቱት ቢሰቅሉት ቢያላግጡበት

ምንም አላገኙም ከርሱ ዘንድ ስህተት

ፈጣሪ መሆኑ ምስጢሩ ገብቷት

ጌታን አልይዝ አለች ግዑዟ መሬት

አዝ---

ይሄ ታላቅ ንጉስ ሲገለጥ በሰማይ

የናቁት የወጉት ይሉለታል ዋይዋይ

ምድርና ሠማይ ከፊቱ ሲሸሹ

ወዴት ልግባ ይላል ትልቁ ትንሹ

አዝ-----

ወደ ላይ ያረገው የከበረው ስጋ

ዳግመኛ መምጣቱን ሁላችን አንዘንጋ

በሰማይ ለሚኖር ቅዱስ አባታችን

ምስጋና ይድረሰው ከኛ ከሁላችን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening