ጠቅላላ

General

ኑ እንቅረብ

Lyrics

ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ /2/

ስጋውን እንብላ /3/ ደሙንም እንጠጣ

የቀራንዮ በግ የአምላክ ስጋው

ተሠውቶልናል እንቀበለው

እድፋን ሀጥያታችን በንስሀ አንፅተው

እንቀበል አምነን በልጅነታችን

መቅረብ ወደ ጌታ በእውነት የሚገባው

በስተ እርጅና አይደለም በወጣትነት ነው

ጨረቃና ፀሀይ ደም ያለቀሱለት

ከዋክብት ሰማይ የተነጠፋለት

ይኽው ተፈተተ እሳተ መለኮት

ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን

ትጋብዛለች ስጋና ደሙን

የአማኑኤል ስጋ ይኽው ተዘጋጀ

ከግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ

መጥቁ ተደወለ እንቅረብ በእልልታ

በኋላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ

ይህችን እድል ፈጥነን እንጠቀምባት

ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይባት

ከአሁኑ እንቅረብ ታውጆአል አዋጁ

የይለፍ ደብዳቤ ስንቅን አዘጋጁ

የህች አለም ጠፊናት በሀብት አትመኩ

ብሏል አምላካችን ተስፋችሁ እንኩ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening