✦
ጠቅላላ
•General
ጌታ ሆይ
Lyrics
ጌታ ሆይ አይሁድ አማፅያን ሰቀሉህ ወይ
የዓለም መድሀኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ/2/
የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመሰቀል
የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት /2/
ንፁህ ክርስቶስ ሆንክ በደለኛ ብለህ ስለእኛ /2/
መስቀል አሸክመው አስረው ገረፋህ እያዳፋህ /2/
እጅና እግርህ በብረት ተመታ የዓለም ጌታ
የእሾህ አክሊል ደፍተህ ጐንህን ተወጋ
አልፋ ኦሜጋ /2/
ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው
ምራቅ እየተፋ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጐዱ/2/
በመስቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል
ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው /2/
ይቅር ባይ ግልፅ በደላችን ሁሎ ሳታይ
አንተው ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.