ጠቅላላ

General

እኔስ በምግባሬ

Lyrics

እኔስ በምግባሬ ደካማ ሆኛለሁ /2/

እዘኝልኝ ድንግል እለምንሻለሁ /2/

ያንን የእሳት ባህር እንዳላይ አደራ

ድረሺልኝ ድንግል ስምሽን ስጠራ /2/

አዝ-----

የዳዊት መሰንቆ የኤልያስ መና

የናሆም መድሀኒት ንኢ በደመና /2/

አዝ-------

አንቺ ነህ ጉልበቴ በደከመኝ ጊዜ

የልቤ መጽናኛ ረዳት ምርኩዜ /2/

አዝ-----

አፈሳለሁ እንባ በጣም ተጨንቄ

እማፀንሻለሁ በደሌን አውቄ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening