ጠቅላላ

General

ታላቁ ጾም ገባ

Lyrics

ታላቁ ጾም ገባ ጾመ ኢየሱስ /2/

በትጋት እንፁም እንድንቀደስ /2/

ጠጃችንን ጥለን ከእንስሳትም ስጋ /2/

መከልከል አለብን እንድናገኝ ፀጋ /2/

ነብዩ ዳንኤል ይሁነን አብነት /2/

መከልከል እንዳለ ከአዝማደ ጥሉላት /2/

ወደ አምላክ ስናዝን በጾማችን ወራት /2/

ሊኖረን ይገባል ፍቅርና አንድነት /2/

መስቀሉን ይዛችሁ ተከተሉኝ ብሏል /2/

ኢየሱስ ክርስቶስ ጾምን ሰርቶልናል /2/

በጾም በጸሎት ብንከተለው /2/

ደቀ መዛሙርቱን መሆናችን ነው /2/

ስለ ወንጌል መራብ መጠማት ስለ ፅድቅ /2/

ብፅዕናን ሰጥቶ ከአምላክ የሚታስታርቅ /2/

መሆኑን ነግሮናል የሁላችን ቤዛ /2/

መስቀሉን ባርኮልን ደሙን እየነዛ /2/

ለመድሀኒታችን በጾም እንገዛ /2/

ሆዳችንን ወደን ሳንኖር በዋዛ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening