✦
ጠቅላላ
•General
በእለተ ዓርብ
Lyrics
በእለተ ዓርብ ስላሴ ሰውን ፈጠሩ ለክብራቸው
የተፈጠሩትም አዳም ሔዋን ናቸው
በጠቅላላው ዓለም ሐይሉ ቢሰጣቸው
አፍርሰው ወደቁ በሰይጣን ተሳስተው
ወይ በደል ወይ ጉደት
የሁላችን አባት አዳም
ያን ጊዜ ጀመረ ለቅሶውን
ተሳስቶ በመብላት እፀ በለስን
ሊወስድ ፈልጐ አምላክነትን
ባልሆነ መካሪ በክፉ ሰይጣን
ወይ በደል ወይ ጉዳት
ከጐኔ ተፈጥረሽ ሄዋን
እንኳን ልትረጂኝ ጐደሺኝ
አንቺ ተሳስተሽ እኔን አሳትሺኝ
በማስመሰል ነግረሽ ስላበላሸኝ
እስከ መቼም ድረስ ሞቼ ቀረሁኝ
ወይ በደል ወይ ጉዳት
አተውቀሰኝ እንጂ አዳም
ምን ላድርግ ብለህ ነው ጌታዬ
ሰይጣን አስቶኝ ነው አዬ መከራዬ
እስከ መቼም ድረስ እሳት ነው ኑሮዬ
ስለተጣላሁኝ ከቸር ፈጣሪዬ
ወይ በደል ወይ ጉዳት
ያቺን ዕፀ በለስ ባትቆርጫት
ከሰይጣን ጋራ ተማክረሽ
የምድሩ ሳይበቃሽ የሰማይ ሽተሽ
እኔን አዋረድሺኝ አንቺም ተዋርደሽ
ከእንግዲህ ይጥቀምሽ ከንቱ ምኞትሽ
ወይ በደል ወይ ጉዳት
ያን ጊዜ ከገነት ሲወጡ
በእሳት ሲገፈፍ ክብራቸው
አንቺ ነሽ አንተ ነህ ሆነ ነገራቸው
ነገር ግን አየጠቅምም መነታሪካቸው
ወይ በደል ወይ ጉዳት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.