ጠቅላላ

General

ሙታንን ያድን

Lyrics

ሙታንን ዘንድ ያድን ዘንድ

የሞት ሞትን ሽሮ ወልደ

አምላክ ሔደ ወደ ኋላ ታስሮ

ግርማን ለኪሩቤል ያጐናፀፋቸው

ዘውድን ለሱራፌል የሚያቀዳጀቸው

ከለሜዳ ለብሶ ዋለ ከፊታቸው

ቅዱሳን እጆቹ አዳምን የሰሩት

ቅዱሳን አግሮቹ በገነት የዞሩት

ተቸንክረው ዋሉ በጠንካራ ብረት

አዳም በበደለ የግፍ ግፍ በሰራ /2/

ቸሩ ወልደ አምላክ ዋለ በመከራ

ምን በበደለ ነው ምን ባደረገ ነው /2/

ወልድ እንደ ቀማኛ ሲገረፈ የዋለው

እኔ ልሙትልህ እኔ ልንገላታ /2/

በተንገላታኸው በተከዝኸው ፈንታ

እንዴት አስታገሰህ በምን ቻለ ሆድ/2/

ትልቁም ትንሹም ሲዘባበቱብህ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening