ጠቅላላ

General

ሞቼ ስለማልቀር

Lyrics

ሞቼ ስለማልቀር ትንሳኤ ስላለኝ

በተስፋ ቤታችን ስለምንገናኝ

ወዳጅ ዘመዶቼ አታልቅሱ በቃኝ /2/

አገኛለሁና ገና አዲሱን ኑሮ /2/

አምላክን አስቡት የብቃችሁ እሮሮ /2/

ይልቅ ፀልዩላት ለነፈሴ እረፍት /2/

በቀኝ እንደያኖራት የጻድቃን አባት /2/

ዓለም ኪራይ ቤት ናት ዘላቂ አይደለችም /2/

ለስጋ ነው እንጂ ለነፍስ አትመችም /2/

ግን በእርሷ ስንኖር ትዕዛዙን ከፈፀምን /2/

ለተዘጋጀው ቤት ወራሾች አኛው ነን /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening