✦
ጠቅላላ
•General
ክርስቶስ በስምህ
Lyrics
ክርስቶስ በስምህ ይዘናል ቀኖና
ስቅለት ትንሳኤህን እናያለን ገና
ጾም ማለት እንግዲህ ይሄ ነው ስርዓቱ
ሐዋርያት ጾመው ለኛ አበረከቱ
ነፈስና ስጋዬ በመብል ተጣለተው
ሽማግሌ ሆኖ ጾም አስታረቃቸው
አብረው እያደሩ አብረው እየዋሉ
አያምርም አይመስልም በመብል ሲጣሉ
ነፍስም ከስጋ ጋር መለየቷን አውቃ
የአለም ተድላዋን ደስታዋን ንቃ
በጾም በሱባኤ ትኖራለች ታጥቃ
ነፍስም ለስጋዋ ትመክረው ጀመረች
በብዙ ምሳሌ እያመሳሰለች
ስጋዬ ሞኝ ነህ መብልን አትውደደው
ከአዳም ጀምሮ ከመጀመሪያው ሰው
መብል ሲጐዳ እንዲ ሲጠቅም መች አየነው
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.