ጠቅላላ

General

ኃጥያቴ በዝቶብኝ

Lyrics

ኃጥያቴ በዝቶብኝ ሸክሜ ቢበዛ

ለእኔ ሀጥያት ብለህ የሆንክልኝ ቤዛ

እኔ በሰራሁት ባጠፋሁት ጥፋት

ለኔ ሀጥያት ብለህ ስትሞት በስቅለት

በዚያች በቀራንዮ በዚያች በጐልጐታ

ያደረክልኝን ያን ታላቅ ውለታ

አረሳውም ፍፁም የኔ ጌታ

ጊዜያዊውን ደስታ ልቤ አለሙን ወዶ

እንዳይቀል በበደል ልቤ በሀጥያት ታርዶ

መንፈስህን ስጠኝ ቃልህ ያስተምረኝ

በልቤ ውስጥ ሆኖ ስቃይህን አሳየኝ

መስቀል ተሸክመህ ስትደፋ ለእኔ

ተራራ ስትቧጥጥ ጌታዬ መድህኔ

እናት እንኳን ለልጅ የሌላት ፍቅር

አሳልፈህ ሰጠህ እጆችህን ለችንካር

ለቀበርዎኝ ጉድጉድ ለወፎች መስፈሪያ

አላቸው ማደሪያ ሌሊት ማሳለፊያ

አንተ ግን ተራቁተህ ለኔ ተዋረድክ

ደግሞ በመስቀል ላይ ሳለ ለኔ መሞትህ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening