✦
ጠቅላላ
•General
ምድረ ቀራንዮ
Lyrics
ምድረ ቀራንዮ ምድረ ጐልጐታ /2/
የአለም መድሀኒት በአንቺ ተንገላታ
መድሀኒት ክርስቶስ ያየብሽ መከራ /2/
ሁሉን ማድረግ ሲችል ስልጣን ሲኖረው /2/
በቀራንዮ መስቀል ፍቅሩ አዋለው /2/
እጆቹ እግሮቹ በችንካር ተመተው /2/
መስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁ እያለ /2/
በእንጨት ላይ ተሰቅሎ ቀራንዮ ዋለ /2/
ደሙ እንደውሀ ሲወርድ በመስቀል ላይ /2/
መከራን ሢቀበል እጅግም ሲሰቃይ /2/
በተራ በተራ ሲፈራረቁበት /2/
በደልን አልሰራም ምንም ዓይነት ስህተት /2/
የእኛን በደል ሀጥያት ክርስቶስ መውሰዱ /2/
ቸሩ መድሀኒዓለም እባክህ ማረን /2/
ከላይ ከዓባትህ ዘንድ ምህረት ላክልን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.