ጠቅላላ

General

በከሀሊነቱ

Lyrics

በከሀሊነቱ በአምላክነቱ /2/

ይቅር ይለናል ይታደገናል /2/ በቸርነቱ

ምን ይከፈለዋል ምን ይሆን ዋጋው

ለፈጠረን ጌታ ለይቅር ባይው

ለድህነት መንገድ ንስሀን የሰራ

እንዳንጠፋበት ነው ዳግም በመከራ

ይቅር ይለናል ይታደገናል /2/ በቸርኑቱ /2/

የሰው ልጅ ከሀጥያት እስኪመለስለት

አይቸኩልም እርሱ መዓትን ለማወረድ

ትዕግስቱ ሰፊ ነው ስራው ረቂቅ

ቸርነት ገንዘቡ ቢሰጠው አያልቅ

ይቅር ይለናል ይታደገናል /2/ በቸርነቱ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening