ጠቅላላ

General

ምን ሰማህ ዮሐንስ

Lyrics

ምን ሰማህ ዮሐንስ በማህፀን ሳለህ /2/

ሕፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /2/

እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /2/

ምን ያለ ፍቅር ነው ምን ዓይነት ሰላምታ /2/

ከተፈጥሮ በላይ ያስገደህ ክብር

እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር /2/

ሌላ ድምጽ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ

ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ/2/

በረሃ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት

ምን ያለ ራዕይ ነው እንዴት ያለ ብስራት /2/

እንደ አዲስ ምስጋና ሥልቱ የተዋበ

ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ /2/

ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳመ

ድንግል ስለሆነ በሕይወቱ ፍፁም /2/

በማህፀን ሳለ ተመርጣ በጌታ

ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening