✦
ጠቅላላ
•General
ሰላምሽ ዛሬ ነው
Lyrics
ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም
ወደ አንቺ መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም/2/
ሆሳዕና በአርያም
እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በኢየሩሳሌም
አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2/
ሆሳዕና እያሉ አመሰገኑት
የኢየሩሳሌም አእሩግ ሕፃናት/2/
ምአህያ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ የገባው
ኢየሡስ ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ነው/2/
ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት/2/
የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.