ጠቅላላ

General

ሆሳዕና በአርያም

Lyrics

ሆሳዕና /2/ በአርያም

ቅድስት ሀገር ሆይ ኢየሩሳሌም/2/

ምስጋናሽ ብዙ ነው/2/ በመላው ዓለም

በአህያ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ የገባው/2/

ኢየሱስ ክርስቶስ /2/ የዓለም መድኃኒት ነው

ኃይልና ስልጣን በአንድ ላይ ስላለው/2/

ጠላቶችሽ ሸሹ /2/ ሕዝብሽም ደስ አለው

እናውቃለን ባዮች ግብዞች ሲቀሩ/2/

ወጣት ሽማግሌ /2/ በአንድ ላይ ዘመሩ

ሰውማ ቢዘምር ምን ያስገርመናል/2/

ሆሣዕና ሰው ቀርቶ /2/ ድንጋይ ይናገራል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening