✦
ጠቅላላ
•General
ሆሳዕና በአርያም
Lyrics
ሆሳዕና /2/ በአርያም
የዘመን ፍፃሜ እስከዚህ የሌለህ/2/
ዘለዓለም የምትኖር /2/ ረቂቅ ምስጢር ነህ
በጣም ደስ ይበልሽ እልል በይ ጽዮን/2/
ንጉስሽ መፃልሽ /2/ ሊሆንሽ መድህን
ተነሽ ተቀበይው እጅሽን ዘርግተሸ/2/
ከኃጥያት ቀንበር /2/ ነፃ ስላወጣሽ
ሕፃናት ምስጢሩ ተገልፆላቸው/2/
ባንድነት ዘመሩ /2/ ለፈጣሪያቸው
ክብር ሆሳዕና ለአምላከ እስራኤል/2/
ተቀምጦ መጣ /2/ በአህያ ግልገል
ትንሹም ትልቁም ፍጥረታት በሙሉ/2/
ምስጋና አቀረቡ /2/ ሆሳዕና እያሉ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.