ጠቅላላ

General

ናና የምስጋና ጌታ

Lyrics

ናና የምስጋና ጌታ

ናና የምህረት ጌታ

ማዳንህ ተገኝታለችና

ሠላምህ ተገኝታለችና

ኢየሩሳሌም ሆይ ምስጋና ጀምሪ

መለከትን ንፊ ነጋሪት ጎስ

ሰላምሽ ታውጇል መዳንሽም ቀርቧል

ጌታ ሊጎበኝሽ ከበር ላይ ቆሟል

ያልታደልሽው ሀገር ጌርጌሲዮን ሆይ

ለምን ተቃወምሽው አምላሽን ስታይ

የከተማውን በር መዝጊያውን ቆልፈሽ

ከሩቅ የሸኘሽው ሲመጣ ሰላምሽ

የቢታንያ ድንጋይ አንደበት አውጥቶ

ምስጋና ጀመረ አምላኩን ለይቶ

ሳርና ቅጠሉ ዘንባባው ሰገደ

ፍጥረት ሊያመሰግን አምላኩን ወደደ

ሕፃን ሽማግሌው ምስጋና ሲያቀርቡ

ተቆልፎ ነበር ፈሪሳዊ ልቡ

ዛሬም በምስጋና ልባችን ይለወጥ

ሆሣዕና ጌታ ይመላለስበት

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening