✦
ጠቅላላ
•General
ሆሣዕና በሉ
Lyrics
ሆሣዕና በሉ ሆሣዕና
ሆሣዕና ብለን እንጀምር ምስጋና
ሆሣዕና በሉ /2/
ለወልደ አምላክ
በአምላክ ስም የመጣ
ስሙ ይባረክ
ትህትናን አሳየን
በትህትና መልክ
ሆሣዕና በሉ /2/
ለሠማይ ንጉስ
ግርማን ለብሶ መጣ
ሕዝቡን ሊቀድስ
ሆሣዕና በሉ ሆሣዕና
ለወልደ ዳዊት
ነቢያት በትንቢት
ለነገሩለት
ሐዋርያት በወንጌል
ለሰበኩለት
ሆሣዕና በሉ /2/
ለአምላከ ምህረት
ተወልዶ ከድንግል
እንደሕፃናት
እረኞች በዋሻ
የሰገዱለት
የአዳም ልጆች ሁሉ
ደግሞም መላዕክት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.