✦
ጠቅላላ
•General
አማኑኤል አምላክ
Lyrics
አማኑኤል አምላክ ምስጋና ይገባሃል
ለአዳም ልጆች ሁሉ ሕይወትን ሰጥተሃል
እልልታ ይገባል ለታላቁ ጌታ
ድንጋዩ ተፈነቃቅሏል
ኢየሱስ በእኩለ ሌሊት በሃይሉ ሞትን ድል
ነስቷል
እሰይ የምስራች እልልታ ለዚህ ይገባል ሽብሸባ ለዚህ ይገባል
የሞት ሀይል ተዋርዷል ዛሬ ሲዖልም
ተመሰቃቅሏል
ደስ ይበለን ባንተ በትንሣኤው ብርሃን /2/
ከለሜዳ ለብሶ እርቃኑን የቆመው እሰይ የምስራች
የእኛ መድሃኒዓለም ሞትን ድል አረገው
ጨረቃና ከዋክብት ደም ያለቀሱለት
ሞትን ድል ለነሣው እናመስግን በእውነት
እውነት በእውነት ጌታ ተነስቷል
ንገሩ ለዓለም ያረገላችሁን
እሰይ የምስራች
ከሲዖል እስራት ያላቀቃችሁን
መላዕክቱም ነጭ ለብሰው ምስራቹን አበሠሩ
ተነሥቷል ኢየሱስ ብለው ለዓለም እንዲናገሩ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.