ጠቅላላ

General

እልል እልል በሉ

Lyrics

እልል እልል በሉ ወዳጆቹ ሁሉ

ሞትን ድል አድርጓል ጌታችን በኃይሉ

ሠባት አጋንንትን ከእኔ ያራቀው

በክብር ተነሥቷል ጌታችን ህያው ነው

ውለታው ታውሶኝ ለእኔ ያደረገው

ማልጄ ብሄድም ሽቶዬን ልቀባው

ታላቅ ቸርነቱ ምህረቱ በዝቶ

ትንሣኤውን አየሁ ሳላስበው ከቶ

የአትክልቱ ጠባቂ መስሎኝ አገኘሁት

ማርያም ባለኝ ጊዜ ጌታዬን አወቅሁት

ያ የፍቅር ድምፁ ገባ ልቦናዬ

ከፊቱ ተደፋሁ መምህር ሆይ ብዬ

ጴጥሮስ ዩሀንስም ሐዋርየት ሁሉ

ሐዘናችሁ ይብቃ እልል እልል በሉ

ኑ እና ተመልከቱ ከመቃብር የለም

ምስራች ንገሩ ሂዱና ለዓለም

ሞትን ድል አድርጓል በሀይል በሥላጣኑ

ህያው ሆኖ የሚኖር ለዘለዓለም

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening