ጠቅላላ

General

ሞት ነው ርኃብ

Lyrics

ሞት ነው ርኃብ ከክርስቶ ፍቅር የሚለየን/2/

ኃይሉ በእኛ ላይ አድሮ እንበረታለን

ፀጋው በእኛ ላይ አድሮ እንበረታለን

ካንተርቀው ሸሽተው እየሔዱ

ጠፋባቸው የፅድቅ መንገዱ

በስጋዊው ጥበብ ሲፈልጉህ

በመታለል ስንቶቹ አንተን አጡህ

አ.ዝ

በተዋህዶ የከበርከው ጌታ

መድሃኒዓለም ሁንልን መከታ

ስንደክም ምኞት ሲፈትነን

ኃይልን ሰጥተህ በእጆችህ ደግፈን

አ.ዝ

የዓለም ሠይፍ በእኛላይ ተስሏል

ስጋችንን ሊቆርጠው አድብቷል

ኃይልን ስጠን እንድናሸንፈው

ፀጋህ ለእኛ የእምነት ጋሻችን ነው

አ.ዝ

ሐዋርያት ፀጋህ በዝቶላቸው

ስለፍቅርህ ፈሰሰ ደማቸው

ዛሬም ለእኛ ፀጋህን አብዛልን

እንዳንደክም ፈተና ሲገጥመን

አ.ዝ

አ.ዝ

ጋሻ ሆነህ እንድትመክትልን

ቸር አምላክ ሆይ ወዳንተ እንጮሀለን

ቢገጥመንም ችግር ወይ መከራ

አትለየን ጌታ ከእኛ ጋራ

ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት

የውኃ ግድግዳ የደም መሠረት/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening