ጠቅላላ

General

እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ

Lyrics

እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ ቸርነት አድርገህ/2/

እድሜን ለንስሐ እንደ ሕዝቅያስ ሰጥተህ

ጠማማውን ልቤን በቃልሀ አቃንተህ

አ.ዝ

አላውቀውም ብሎ ሲጠየቅ ያፈረው

ዶሮ እስኪጮህ ድረስ ሶሰት ጊዜ የካደው

የጅረት ወንዝ ነው የሰጠኸው እንባ

ጴጥሮስ ተጸፅቶ ንስሐ እንዲገባ

ጽዋው እንዳይደርሰኝ የይሁዳ እድል

ልጅህ ሆኖ ውሎ ማታ መኮብለል

ጴጥሮስ እድለኛው አልቅሶ ተማረ

በትዕቢቱ ይሁዳ እንደወጣ ቀረ

አ.ዝ

አ.ዝ

ዘመኗን በሙሉ በዝሙት አቃጥላ

ለንስሐ ጠራት ጌታ በገሊላ

ታድሳ ተነሳች በእንባዋ ብዛት

እግሩስር ተደፍታ ማርያም መግደላዊት

አመፀኛው ልቤ ዛሬስ መች ይተኛል

በሀሳብ በዝሙት በስርቆት ይዋኛል

ወደቀድሞው ግብሩ እንዳይመለስ

ፍቅርህ በኔ ፀንቶ ኃጥያቴን ደምስስ

አ.ዝ

አ.ዝ

በደላችንን ሁሉ ሳታስብ ትተህ

በምጽአትህ ሰዓት ከፃድቃን ቆጥረህ

ነጭ ልብስን ለብሰን ሆነን ካንተ ጋራ

በሩ ሳይዘጋ አስገባን አደራ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening