ጠቅላላ

General

ማን እንደእርሱ

Lyrics

ማን እንደእርሱ እንደ እግዚአብሔር

ቸርነቱ ብዙ በሰማይ በምድር

አ.ዝ

ሞገድና ንፋስ የሚታዘዙለት

አብርህት ቀላያት የመሰከሩለት

ኅቱም መቃብርን ሳይከፍት የተነሳ

ነፍሳትን ያዳነ ከሲዖል አበሳ

ፈዋሴ ድውያን ቸርነቱ ብዙ

የፀጋ ልብሳቸውን ጽድቅን ለታረዙ

የተዋረዱትን ከፍ ከፍ የሚያድርግ

ለባልቴቷ ዳኛ ፈራጅ ለድን አደግ

አ.ዝ

አ.ዝ

የጠፋውን አዳም ሊፈልግ የመጣ

ከባርነት ዓለም ከፅልመት ያወጣ

ከብርሃን ካባ ጨለማን ያራቀ

ሰውን ከራሱ ጋር ሞቶ ያስታረቀ

በመከራ ሳለን ሕዝቦቹን ያሰበን

ሥጋውና ደሙን ቆርሶ የመገበን

የከበረ ዳኛ ምህረቱ የበዛ

ጌታችን እርሱ ነው የሁላችን ቤዛ

አ.ዝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening