✦
ጠቅላላ
•General
አማን በአማን
Lyrics
አማኑኤል ተመስገን
ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበል
ድብቁን ኃጢያት አንተ ብትገልጠው
ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው
እንደሰው በቀል ቢኖርህ ጌታ
ለእኔስ ኃጥያት የለውም ቦታ
አ.ዝ
በየደቂቃው ኃጥያት ስሰራ
ስሰርቅ ስበድል አንተን ሳልፈራ
አንተግን ፊትህ ምንም ቢቀየም
በቁጣህ በትር አልቀሰፍከኝም
አ.ዝ
አ.ዝ
ምህረትን ልከህ አድነኝ ዛሬ
ታክቶኛልና በኃጥያት መኖሬ
ዓለም በኃጥያት እየሳበችኝ
በጽድቅህ ደስታ መኖር አቃተኝ
የኃጥያት ጉዞ ጣፋጭ ቢመስልም
ውጤቱ መርሮ ፍፁም አይጥምም
እንደበደሌ ስላልከፈልከኝ
ተመስገን እንጂ ሌላስ ምን አለኝ
አ.ዝ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.