ጠቅላላ

General

እውቀት ጥበብ

Lyrics

እውቀት ጥበብ የምገበይባት/2/

ሰንበት ትምህርት ቤቴን አምላክ ይጠብቃት

እውቀት ጥበብ የምገበይባት

አሳድጋኛለች በማር በወተት

እቅፍ ድግፍ አርጋ እንደ እናት አባት

በፃድቁ አባቴ ምልጃና ፀሎት

ይኸው ደርሻለው ለዛሬዋ እለት

አ.ዝ

ምሥጢረ ስላሴ የእምነቴ መሠረት

ከአባቶች ተምሬ የተረዳሁባት

ምግባር ከሃይማኖት ያስተባበርኩባት

የዕውቀት ገበያ ገነተ ኢየሱስ ናት

አ.ዝ

የዓለሙ ሞገድ ሲበዛ ፈተና

ፍፃሜ እንዲኖረን በእምነት እንድፀና

ገብረ መንፈስ ቅዱስ በምልጃህ ቶሎ ና

እኛ ስጋውያን ደካሞች ነን እና

በመስቀልህ ባርከን ቅዱስ አባታችን

ፀጋህ ይደርብን በእኛ በሁላችን

ማህበራችንን ጠብቅ ለዘለዓለም

ልጆችህ እንድንኖር በፍቅር በሰላም

አ.ዝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening