ጠቅላላ

General

ወይቤሎሙ ሁሩ

Lyrics

ወይቤሎሙ ሁሩ ወመሀሩ ለዘኢይአምን

ወንጌለ መንግስተ ሰማያት/2/

አ.ዝ

በሕይወታችሁ ስበኩ በኑሮአችሁ

ከፅንፍ እስከፅንፍ

በዓለም ዙርያ አዳርሱ ሳትሰለቹ

ደመናን ጠቅሳችሁ እንደ ወፍ

በኃጥያት ገመድ ተይዞ ለታሰረው

በዓለም ጽልመት ለተዋጠው

የእውነት መንገድ ብርሃኑ ለጠፋበት

በሁለንተናው ፈንጥቁበት

አ.ዝ

የጽድቅ እንጀራ በማጣት ለተራበው

የሕይወትን ውኃ ለተጠማው

ቀቢፀ ተስፋ በልቡ ላደረበት

አ.ዝ

የወንጌል ማዕድ አቅርቡለት

አርድእተ ወንጌል ካህናት ሊቃውንት

ለተልእኮ የጠራችሁ

ከእውነተኛው ምነጭ ከጌታ ከበዓሉ

የሕይወትን ውኃ የጠጣችሁ

አ.ዝ

ሁለንተናችሁ ይነበብ ወንጌል ይሁን

በትዕዛዙ ሄዳችሁ

ስራችሁ ይብራ በዓለም እንደሻማ

በሕይወታችሁ ሰብካችሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening