ጠቅላላ

General

የሥላሴ መንበር

Lyrics

የሥላሴ መንበር ቅዱሳን ከበውት

ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት

ድንግልን ከመሀል ሚካኤልን ከፊት

አእላፍ መላእክት ሲሰግዱ በፍርሃት

እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት(አባት)

የሥላሴ መንበር ቅዱሳን ከበውት

እያሸበሸቡ የሰማይ መላእክት

ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ

ይህን ታላቅ ክብር ሊያዩ የታደሉ

በጽድቅ ስራቸው ደምቀው ይታያሉ

የቅዱሳን ህብረት የቅዱሳን ሀገር

ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር

ፍቅርና ርህራኄ የተመላ ሰማይ

እግዚአብሔር ያድለን በትንሣኤ እንድናይ/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening