ጠቅላላ

General

መድኃኔዓለም

Lyrics

መድኃኔዓለም አንተን ማን ይመስላል

የከበደን በስምህ ይቀላል

የማትችለው የለም የሚሳንህ ነገር

ቀላያት አይጸኑም አንተ ስትናገረ

አልቅሼ ነገርኩህ በሀዘን ደክሜ

አብዝቼ ጠራሁህ ከመቅደስህ ቆሜ

አዘነበልክልኝ ቃሌን መች አለፍከው

አይዞሽ ልጄ ብለህ እንባዬን አበስከው

አዝ=====

ከፊት እየቀደምክ መንገድ የምትመራ

ብርሀን የሆንክልን በመስቀልህ ስራ

እውነተኛ መድህን የሕይወት እንጀራ

የሁሉ አስገኚ ግሩም የእጅህ ስራ

አዝ=====

ያላለፍኩት የለም አንተን ተጠግቼ

መጽናቴ በአንተ ነው ስምህን ጠርቼ

የበረከቴ ምንጭ የጎጆዬ ሙላት

ለደከመች ነፍሴ ማረፊያ ሆንክላት

አዝ=====

ዳግም ልጅህ ተባልኩ በደሌን ሻርክልኝ

በከበረው ደምህ ባርያህን ገዛኸኝ

ሳወድስህ ልኑር ዘውትር በዝማሬ

መድኃኔአለም ሆንከኝ ሞገሴ እና ክብሬ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening